Monday, November 2, 2009

የአራት ፓርቲዎች ስምምነት ወይስ የሁለት ፓርቲዎች ስምምነት!?

ሰሞኑን ኢህአዴግ ከመኢአድ፤ ከኢዴፓ እና ከአየለ ጫሚሶው ቅንጅት ጋር የምርጫ ስነ ምግባር መመርያና ደንብ ተፈራርሟል:: ጉዳዩም ብዙ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው:: በተለይ የኢንጅነር ሃይሉ ከመለስ ዜናዊ ጋር ተጨባብጠው የፊርማውን ሰነድ መረካከብ ብዙ እያስባለ ነው:: አንዳንዶች ትላንት ካሰራቸውና ደጋፊዎቻቸውን ከገደለው አምባገነኑ መለስ ጋር እንዲህ አይነት ስምምነት መፈራረም አልነበረባቸውም ሲሉ ሌሎች ደግሞ እየተከተሉት ካለው ሰላማዊ የፖለቲካ አማራጭ አንፃር ሌላ አማራጭ የላቸውም ይላሉ:: የመኢአድ አባላት መድረክን መቀላቀል አይፈልጉም:: ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው ያለፈው የቅንጅት ተሞክሯቸው ነው:: በተለይ ደግሞ የትናንቱ የወያኔ ቱባ ባለስልጣንና በርካታ የአማራ ብሄረሰብ አባላት ከበደኖው የአማሮች እልቂት ጀርባ እጁ አለበት ብለው የሚያምኑት ስዬ አብርሃ ከጀርባ ሆኖ ከሚያሽከረክረው መድረክ ጋር መቀላቀልን አይፈልጉም:: ይሄ ማለት መኢአድ የስዬ መድረክ ሲያኮርፍ ማኩረፍን እንደ ውርደትና ክህደት ቆጠረው::ለዚህም ነው በምርጫ መሳተፍ አላ ማዬ እስካለ ድረስ መደራደርን አላማው ያደረገው:: የድርድሩ ውጤት ምንም ይሁን ምን ከመድረክ ጋር አብሮ ከመስራት ከዋናው ወያኔ ጋር መደራደር ይሻላል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች:: አስተያየት ሰጪዎቹ ድርድሩ የተካሄደው ግን በሁለት ፓርቲዎች መካከል ነው ይላሉ::

No comments:

Post a Comment